ስለ ኧሌ ህዝብ

Awkaro

ይህ ድህረ ገጽ የኧሌ ባህልና ቋንቋ ድህረ ገጽ ነዉ። ኢትዮጵያ የብዙ የተለያዩ ባህልና ቋንቋ ያላቸው ብሔረሰቦች ቤት ናት። የኧሌ ብሔረሰብ በደቡብ ኢትዮጵያ ካሉት 56 ብሔረሰቦች አንዱ ነዉ። ከ 1987 ዓ.ም ጀምሮ ሰባት የኧሌ ገበሬ ማህበራትት ከኮንሶ ልዩ ወረዳ ጋር ስተዳደሩ በአሥር ቀበለያት ያሉት የገበረ ማህነራት ከዴራሼ ልዩ ወረዳ ጋር ስተዳደሩ ነበር። መንግሥት ለማስተዳደር ያመቻቸዉ ዘንድ በመከፋፈል ከኮንሶ ጋር የነበሩትን "ገዋዳ" ብለዉ ስጠሩ ከደራሼ ጋር የነበሩትን ዶባሰ ተብለዉ ይጠራሉ። ነገር ግን በህዝቡ ዘንድ በእነዚህ አሥራ ሰባት ቀበለያት ያለዉ ህዝብ ኧሌ በመባል ይታወቃል። 'ኧሌ" የሚለዉ ቃል ስተረጎም አብሮ መሆን፤ ህዝብ ወይም በደጋማ አከባቢ የምኖር ህዝብ ማለት ነዉ። ስለዚህ ለኧሌ ብሔረሰብ ኧሌ የሚል ስያሜ የተሰጠዉ መጀመሪያ ላይ ኧዉጋሮ የተባለ ደጋማ አከባቢ በመስፈሩ ነዉ።በ ቀን 20/05/2000 ዓ.ም በቁጥር 22/000231/3545 የተጻፈዉ የመንግስት ደብዳቤ እንደምያመለክተዉ የኧሌ ብሔረሰብ "ኧሌ ወረዳ" በማለት በራሱ ማንግስታዊ መዋቅር እንድተዳደር ተወስኗል። 

የኧሌ ህዝብ በደጋማና ቆላማ አከባቢ የሰፈረ ስሆን በደቡብና በምስራቅ ከኮንሶ ጋር፥ በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ ከዴራሼ ጋር እንድሁም በምዕራብ ከፀማይ/ደቡብ ኦሞ/ ጋር ይዋሰናል። ይህ ካርታ የኧሌ ህዝብ የሰፈሬበትን አከባቢ  በግምት   የምያመለክት ስሆን የኧሌ ህዝብ ከኢትዮጰያ በስተደቡብ በኩል በኮንሶ፤ ድራሸና ደቡብ ኦሞ ዞን ጋር ይዋሰናል።  የኧሌ ህዝብ ለረጀም ዘመናት ለሁለት ተካፍሎ ብቆይም በህዳር 23/203 ዓ.ም  ራስን በራስ ማስተዳድር እድል ማግኝት ችሏል። የኧሌ ወረዳ ቆዳ ስፋት103891.9637km ያህል ስሆን አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር በ2000 ዓ.ም በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ 68600 ያህል ደርሶዓል። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ 85137 በላይ ይሆናል ተብሎ ይገመታል። 

Your encouragement is valuable to us

Your stories help make websites like this possible.